Tuesday, September 10, 2013

ባሕረ ሐሳብ

እንኳን ለ፳፻፮ /2006/ ዓመተ ምህረት ዘመነ
ማርቆስ በሰላም በጤና አደረስዎ!

Ø  ባሕረ ሐሳብ ከሁለት የግዕዝ ላት የተገኘ ሲሆን
ባሕር  =  ዘመን
ሀሳብ  =  ቁጥር ማለት ነው። /ዝርዝሩን ከብሎጉ ይመልከቱ/ 

ባሕረ ሐሳብ ማን ደረሰው ?
Ø  የእስክንድርያ 12 ሊቀ ጳጳስ (ፓትርያርክ) የነበረው ቅዱስ ሜጥሮስ
180 – 222 . ድረስ 42 ዓመት ሊቀ ጳጳስ ነበር። ሊቀጳጳስ ከመሆኑ በፊት መስተገብረ ምድር (ገበሬ) ነበር። አርቆ በአጭር ታጥቆ የሚሰራ ትጉህ ገበሬ ነበር። ከልዕልተ ወይን (የቤተክርስቲያን ለቃውንት የሚጠሯት ስም) ጋር አጋብተዋቸው ነበር።
የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ ዩልዩስ (ዩልያኖስ) ሹሞታል።  /ሙሉ ታሪኩን ብሎጉን ይጎብኙ/

ባሕረ ሐሳብ በመጽሐፍት ቤት
Ø  ቤተ ክርስቲያን አራት ጉባዔ ቤቶች አሏት
·         ብሉይ ኪዳን
·         ሐዲስ ኪዳን
·         መጽሐፈ መነኮሳት (ማር ይስሐቅ፣ ፈልክዲዳዩስ)
·         ሊቃውንት (ሃይማኖተ አበው)
·         አምስተኛ ጉባዔ  ተደርጐ በሁለት መንገድ ይሰጣል። አቡከክር (አቡካኻር) ባሕረ ሀሳብ ተብሎ
Ø  አቡካኻር (ወልደ አቤል ሄሬም) የተባለ መነኩሴ ሲሆን ባሕረ ሐሳብን ጨምሮ ሌሎች የሥነ ጸሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት ሊቅ ነው። ባሕረ ሀሳብም አብሮ ተገልጾለታል።


Ø  ከዲሜጥሮስ በተጨማሪ ባሕረ ሀሳብን ለማወቅ የተመኙ
1.   ሰዒድ ወልደ ጰጥሪቅ
2.   መሀቡብ ወልደ መንጋ
3.   ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
4.   ኤጲፋን ዘመንፈስ ቅዱስ
5.   ጊዮርጊስ ወልደ አሚድ
6.   ማርቆስ ወልደ ቀምበር
7.   ዮሐንስ ወርል ልሔሬም (አቡካክር)እና ሌሎችም

የቅዱስ ድሜጥሮስ ምኞት  
Ø  በዓላትና አጽዋማት ከጥንተ ዕለታቸው ባይጡ ባይነዋወጡ እያለ ይመኝ ነበር። ይኸውም
·         ጾመ ነነዌ፣ ዐብይ ጾም፣ ጾመ ሐዋርያት፣  ከሰኞ
·         በዓለ ርክበ ካህናት፣ ጾመ ድኅነት ከረቡዕ
·         በዓለ ዕርገት ሐሙስ
·         በዓለ ደብረ ዘይት፣ ሆሳዕና፣ ትንሳኤ፣ ጰራቅሊጦስ ከእሁድ

Ø  መልአከ እግዚአብሔር ነገረ በምኛት አይሆንም ሱባዔ ገብተህ አግኘው አለው
          ከሌሊቱ 23 ሱባዔ ገብተህ አበቅቴ
          አቀኑ 7 ሱባዔ መጥቅዕ ይሁንህ ብሎታል
ምነው ሌሊቱን አብዝቶ ቀኑን አሳነሰው? / ከብሎጉ ይመልከቱ/
          23 ሱባዔ ማለት
          1 ሱባዔ = 7 ቀናት
          23 ሱባዔ = ?
          161 ቀናት
አዋጅ  ማንኛውም ቁጥር 30 30 ግደፈው
          161 ÷ 30 = 5 ደርሶ 11 ይቀራል
          11 ጥንተ ቅቴ ይባላል።
ሰባት ሱባዔ ማለት
          1 ሱባዔ = 7
          7 ሱባዔ = ?
          7× 7= 49
30 ስንገድፈው (49÷30) =1 ደርሶ 19 ይቀራል
          19 ጥንተ መጥቅዕ ይባላል።
መጥቅዕና አበቅቴ ተደምረው 30 አይበልጡም 30 አያንሱም
አዋጅ  “በቅ ወመጥቅዕ ክልዔሆሙ ኢየዓ እም፴ ይወርዱ እም፴  ወትረ ይከውኑ ”  ይላል።
ሕዝቡስ ሜጥሮስ በፊት እንዴት ያከብር ነበር?
                  
አዕዋዳት
አዕዋድ ከሚል የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ዞረ ማለት ሲሆን በየጊዜው እየዞረ የሚመጣ ማለት ነው።
ዓመተ ዓለም የሚሠርበት ሰባት አዕዋዳት አሉ። እነሱም፦
Ø  ዓውደ ዕለት - እሁድ
Ø  ዓውደ ወርኅ በፀሐይ 30 ቀናት በጨረቃ 29 30
Ø  ዓውደ ዓመት- በፀሐይ 365 ቀናት 6 ሰዓት (15 ኬክሮስ) በጨረቃ 354 22 ኬክሮስ
Ø  ዓውደ አበቅ (ንዑስ ቀመር) = 19 ዓመት
Ø  ዓውደ ፀሐይ = 28 ዓመት
Ø  ዓውደ ማኅተም (ማዕከላዊ ቀመር) = 76 ዓመት
Ø  ዓውደ ዐቢይ ቀመር (ዐቢይ ቀመር) = 562

ወንበር
·         የዘመኑን አበቅቴንና መጥቅዕ የሚያስገኝ ነው።
·         ወንበር ለማግኘት ቀድመን ዓመተ ዓለሙን ማውጣት
          5500 ዓመተ ፍዳ፣ ዓመተ ኩነኔ
          2006 ዓመተ ምህረት ዓመተ ሥጋዌ (ለምን ዓመተ ምህረት ተባለ?)
            በድምሩ 7506
ይህንና በሶስቱ ቀመሮች እንቀምረዋለን።
·         ቀመር    532
·         ከላዊ ቀመር 76
·         ንዑስ ቀመር፣    19
1. ለዐ ቀመር
          7506 ÷ 532
          14 ቀመር 7448 ሆኖ 58 ይቀራል
2. ለማከላዊ ቀመር
          58 ከላዊ ቀመር (76) አይችልም
3. ለንዑስ ቀመር
          58÷19= 3 ጊዜ ደርሶ 1 ይቀራል
አዋጅ  “አሐደ አዕት ለዘመን  - አንድ ለዘመኑ ስጥ
Ø  ለምን አንድ እንቀንሳለን? /ከብሎጉ ይመልከቱ/
          1 -- 1 ዜሮ
2006 .. ወንበር ዜሮ ይሆናል
2009 ሥራ?
Ø  ቅቴ  ከሚል የግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን
·         ተረፈ ዘመን
·         ቁጥረ ሌሊት
·         ሌሊት ማለት ነው።

Ø  አበቅቴን ለማግኘት
          ጥንተ አበቅቴ ከወንበር ጋር ማባዛት
          30 ከበለጠ - 30 መግደፍ
ቅቴ = 11 × 0 = 0 ( አልቦ አበቅቴ ይሆናል)
Ø  ይህ ማለት ፀሐይና ጨረቃ በተፈጠሩበት ስኮ ተገኝተዋል ማለት ነው

Ø  አበቅቴ የሚጠቅመን ሌሊቱን ለማግኘት ነው።
·         ሌሊት = ዕለት + አበቅቴ + ሕፀጽ
ሕፀጽ
- ጐደለ
ሕፀ - ጉድለት ማለት ነው።
ጨረቃ ከፀሐይ የምታጐድለው ማለት ነው።
የዓመቱ ሕፀጽ፦
·         የመስከረምና የጥቅምት = 1
·         የሕዳርና ታህሣሥ= 1 ከላይኛው ጋር = 2
·         የጥርና  የካቲት =     3
·         የመጋቢትና የሚያዚያ =
·         የግንቦትና የሰኔ =       5
·         የሐምሌና የነሐሴ = 6
·         ጳጉሜ ወር ስለማትሞላ 6 ነው።
·         የመስከረም 1/2006 . ሌሊት፦ቸቸ
          ዕለት + ቅቴ + ሕፀጽ
          1 + 0 + 1 = 2
          ጳጉሜ አምስት ማታ በተክቦ አድረዋል።

መጥቅዕ
·         ደወል ማለት ነው
ደወል ሲመታ የራቁ ይቀርባሉ፣ የተበተኑ ይሰበሰባሉ ይህም መጥቅዕ በዓላትና አጽዋማትን ይሰበስባል።
የዘመኑን መጥቅዕ ለማግኘት ጥንተ መጥቅዕን ከወንበር ጋር ማባዛት
·         30 ከበለጠ 30 ማካፈል ነው
19 × 0 = 0
ነገር ግን አበቅቴው = 0 ስለሆነ በአዋጃችን (ወትረ ይከውኑ 30) ስለሚል የዚህ ዓመት መጥቅዕ 30 ይሆናል።
በሌላ ቋንቋ አበቅቴው ዜሮ ከሆነ ሁልጊዜም መጥቅዕ 30 ነው።

ሐመር
·         ባጀ - ቆየ ሰነበተ
·         ሐመርመርከብ
 በዓላትና አጽዋማት የሚያሰነብት ስለሆነ መባጃ ሐመር ተብሏል።

መባጃ ሐመርን ለማግኘት
·         መጥቅዕና በዓለ መጥቅዕ የዋለበትን የዕለት ተውሳ መደመር ነው።
          30 ከበከጠ 30 መግደፍ
በዓለ መጥቅዕ መቼ ይውላል?
አዋጅ መጥቅዕ 14 በላይ ከሆነ በመስከረም
            14 በታች ከሆነ በጥቅምት
          (መጥቅዕ ሲበዛ ከመስከረም ንዛመጥቅዕ ሲያንስ ጥቅምትን ዳስ)
            መጥቅዕ 30 ነው ( 30 > 14)
በዓለ መጥቅዕ በመስከረም (በመስከረም 30) ቀን ይውላል።

የዕለት ተውሳክ
·         ተውሳክ  -    ወሰከ - ጨመረ
-       ጭማሪ ማለት ነው።
·         የቅዳሜ ተውሳክ -  8
·         የእሑድ    -       7
·         የሰኞ       -       6
·         የማክሰኞ   -       5
·         የረቡዕ     -       4
·         ሐሙስ     -       3
·         ዓርብ      -       2
መስከረም 30/2006 . . ሐሙስ ይውላል (3 ተውሳክ)
ባጃ ሐመር = መጥቅዕ + የዕለት ተውሳክ
          30 + 3 = 33
          30 ሲገደፍ = 3

የመባጃ ሐመር ጥቅም
ከበዓላትና አጽዋማት ተውሳክ ጋር በመደመር የየዘመኑንን በዓላትንና አጽዋማት ያስገኝልናል።
የበዓላትና አጽዋማት ተውሳክ የሚውልበት
          1. ጾመ ነነዌ  ተውሳክ የላትም (0 ነው)
                 ስለዚህ መባጃ ሐመር ብቻውን ይመራታል
አዋጅ በዓለ መጥቅዕ በመስከረም ከዋለ ጾመ ነነዌ በጥር ትገባለች
           በዓለ መጥቅዕ በጥቅምት ከዋለ ጾመ ነነዌ በየካቲት ትገባለች
            በዓለ መጥቅዕ በመስከረም 30 ከዋለ በጥቅምት ትገባለች
ዘንድሮ አልቦ አበቅቴ ሆኖ በመስከረም 30 በዓለ መጥቅዕ ስለዋለ ጾመ ነነዌ በየካቲት ትገባለች።
       2. የዐቢይ ጾም ተውሳክ   = 14
       3. የበዓለ ደብረ ዘይት     = 11
       4. የበዓለ ሆሳዕና         = 2
       5. የበዓለ ስቅለት         = 7
       6. የበዓለ ትንሣኤ        = 9
       7. የበዓለ ርክበ ካህናት    = 3
       8. የበዓለ ዕርገት          = 18
       9. የበዓለ ጰራቅሉጦስ      = 28
       10. ጾመ ሐዋርያት         = 29
       11. ጾመ ድኅነት            = 1
                   
በዓላትና አጽዋማት
1.   ጾመ ነነዌ መባጃ ሐመር ተውሳክ የላትም
3 + 0 = የካቲት 3
2.   በዐተ ዐቢይ ጾም 3 + 14 = 17
                    የካቲት = 17
3.   ደብረ ዘይት  3 + 11 = 14
                   መጋቢት 14
4.   በዓለ ሆሳዕና  3 + 2 = 5
                   ሚያዚያ 5 (እሁድ)
5.   በዓለ ስቅለት 3 + 7 = 10
                  ሚያዚያ 10 ( አርብ)
6.   በዓለ ትንሣኤ 3 + 9 = 12
                   ሚያዚያ 12 (እሁድ)
7.   በዓለ ርክበ ካህናት 3 + 3 = 6
ግንቦት 6
8.   በዓለ ዕርገት      3 + 18 = 21
                 ግንቦት 21 (ሐሙስ)
9.   በዓለ ጰራቅጦስ  3 + 28 = 31
                   30 ሲገደፍ 1 ይቀራል
                   ሰኔ 1 (እሁድ)
10.               ጾመ ሐዋርያት 3 + 29 = 32
                  ሰኔ 2 (ሰኞ)
11.               ጾመ ድኅነት   3 + 1 = 4
                   ሰኔ 4 (ረቡዕ)
ኢየዓርግና አይወርድ
·  ጾመ ነነዌ ከጥር 17 አትወርድም ከየካቲት 21 አትወጣም

የተረሱ ወይም ወደፊት የምንፈልጋቸውን ቀናትን ማግኘት

ለምሳሌ 2006 በዓለ መጥቅዕን ለማግኘት ብንፈልግ

 መስከረም 30/2006
· 
1.  1. ወንጌላውያኑን ማግኘት
       ዓመተ ፍዳ + . .
       5500 + 2006 = 7506
ዓመተ ዓለሙን 4 ወንጌላውያን በማካፈል
·         ቀሪው 1 ከሆነ    ማቴዎስ
·         2 ከሆነ           ማርቆስ
·         ከሆነ           ሉቃስ
·         ከሆነ           ዮሐንስ
7506 ÷ 4 = 1876 ደርሶ 2 ይቀራል
          ንጌላዊው  ማርቆስ

2. መስከረም 1 ( ዕለተ ቀመር)
          ዓመተ ዓለም + መጠነ ራብዒት = ለሰባቱ ዕለታት ማካፈል
            7506 + 1876 = 9382
            9382 ÷ 7= 1340 ደርሶ 2 ይቀራል ቀሪ
·         1 ከሆነ = ማክሰኞ
·         2 ከሆነ = ረቡዕ
·         3 ከሆነ = ሐሙስ
·         4 ከሆነዓርብ
·         5 ከሆነ = ቅዳሜ
·         6 ከሆነ = እሁድ
·         0 ከሆነሰኞ
3 . ዕለቱን ለማግኘት
       ዕለት + አጽፈ ወርኅ + ጥንተ
       መስከረም 30 + የመስከረም እጥፍ + ጥንተ ዮን
ጥንተ ዮን መስከረም 1 ረቡዕ ከዋለ = ጥንተ ዮን አንድ ነው።
·         ሐሙስ ከዋለ   = 2
·         ዓርብ ከዋለ    = 3
·         ቅዳሜ ከዋለ   = 4
·         እሑድ ከዋለ   = 6
·         ሰኞ ከዋለ      = 7
·  መስከረም 1 ቀን ረቡዕ ስለዋለ ጥንተ ዮን አንድ ነው።
             ዕለት + አጽፈ ወርኅ + ጥንተ ዮን
              30 + 2 + 1 = 33
33ን ለሰባት ማካፈልና ቀሪው
·  1 ከሆነ    እሁድ
·  2 ከሆነ    ሰኞ
·  3 ከሆነ    ማክሰኞ
·  4ከሆነ     ረቡዕ
·  5 ከሆነ     ሐሙስ
·  6 ከሆነ    ዓርብ
·  0 ከሆነ     ቅዳሜ
                   33 ÷ 7= 4  ጊዜ ደርሶ 5 ይቀራል
                   መስከረም 30 ሐሙ ይውላል
       የቤት ስራ
1.  የአድዋ ድል መቼ ነበር ?
2. ጌታ የተጠመቀበት መቼ ነበር?
3. የ2010ን በዓለ ትንሳኤንና በዓለ ርክበ ካህናትን አውጣ!


በቀጣይ አንደተለመደው ካቆምንበት እንቀጥላለን። የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን!
























2 comments:

  1. አድሜና ጸጋውን አሙሉቶ አስፍቶ ይስጥልን። ይበርቱ

    ReplyDelete
  2. bedend altebraram bizu example binor tiru new
    egziabher yistilen

    ReplyDelete

Thank you for your comments, we will response on timely manner.
thank you again.