Thursday, September 11, 2014

እንኳን ለ፳፻፯ /2007/ ዓመተ ምህረት ዘመነ
     ሉቃስ በሰላም በጤና አደረስዎ!


ባሕረ ሐሳብ
Ø  ባሕረ ሐሳብ ከሁለት የግዕዝ ላት የተገኘ ሲሆን
ባሕር  =  ዘመን
ሀሳብ  =  ቁጥር ማለት ነው። /ዝርዝሩን ከብሎጉ ይመልከቱ/
ባሕረ ሐሳብ ማን ደረሰው ?
Ø  የእስክንድርያ 12 ሊቀ ጳጳስ (ፓትርያርክ) የነበረው ቅዱስ ሜጥሮስ
180 – 222 . ድረስ 42 ዓመት ሊቀ ጳጳስ ነበር። ሊቀጳጳስ ከመሆኑ በፊት መስተገብረ ምድር (ገበሬ) ነበር። አርቆ በአጭር ታጥቆ የሚሰራ ትጉህ ገበሬ ነበር። ከልዕልተ ወይን (የቤተክርስቲያን ለቃውንት የሚጠሯት ስም) ጋር አጋብተዋቸው ነበር። /ሙሉ ታሪኩን ብሎጉን ይጎብኙ/
የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ ዩልዩስ (ዩልያኖስ) ሹሞታል።  
ባሕረ ሐሳብ በመጽሐፍት ቤት
Ø  ቤተ ክርስቲያን አራት ጉባዔ ቤቶች አሏት
·         ብሉይ ኪዳን
·         ሐዲስ ኪዳን
·         መጽሐፈ መነኮሳት (ማር ይስሐቅ፣ ፈልክ)
·         ሊቃውንት (ሃይማኖተ አበው)
·         አምስተኛ ጉባዔ  ተደርጐ በሁለት መንገድ ይሰጣል። አቡክር (አቡኻር) ባሕረ ሀሳብ ተብሎ
Ø  አቡኻር (ወልደ አቤል ሄሬም) የተባለ መነኩሴ ሲሆን ባሕረ ሐሳብን ጨምሮ ሌሎች የሥነ ጸሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት ሊቅ ነው። ባሕረ ሀሳብም አብሮ ተገልጾለታል።

Ø
  ከዲሜጥሮስ በተጨማሪ ባሕረ ሀሳብን ለማወቅ የተመኙ
1.   ሰዒድ ወልደ ጰጥሪቅ
2.   መሀቡብ ወልደ መንጋ
3.   ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
4.   ኤጲፋን ዘመንፈስ ቅዱስ
5.   ጊዮርጊስ ወልደ አሚድ
6.   ማርቆስ ወልደ ቀምበር
7.   ዮሐንስ ወርል ልሔሬም (አቡካክር)እና ሌሎችም
የቅዱስ ድሜጥሮስ ምኞት  
Ø  በዓላትና አጽዋማት ከጥንተ ዕለታቸው ባይጡ ባይነዋወጡ እያለ ይመኝ ነበር። ይኸውም
·         ጾመ ነነዌ፣ ዐብይ ጾም፣ ጾመ ሐዋርያት፣  ከሰኞ
·         በዓለ ርክበ ካህናት፣ ጾመ ድኅነት ከረቡዕ
·         በዓለ ዕርገት ሐሙስ
·         በዓለ ደብረ ዘይት፣ ሆሳዕና፣ ትንሳኤ፣ ጰራቅሊጦስ ከእሁድ

Ø  መልአከ እግዚአብሔር ነገር በምኞት አይሆንም ሱባዔ ገብተህ አግኘው አለው 
          ከሌሊቱ 23 ሱባዔ ገብተህ አበቅቴ
          ቀኑ 7 ሱባዔ መጥቅዕ ይሁንህ ብሎታል
ምነው ሌሊቱን አብዝቶ ቀኑን አሳነሰው? /ከብሎጉ ይመልከቱ/
          23 ሱባዔ ማለት
          1 ሱባዔ = 7 ቀናት
          23 ሱባዔ = ?
          161 ቀናት
አዋጅ  ማንኛውም ቁጥር 30 30 ግደፈው
          161 ÷ 30 = 5 ደርሶ 11 ይቀራል
          11 ጥንተ ቅቴ ይባላል።
ሰባት ሱባዔ ማለት
          1 ሱባዔ = 7
          7 ሱባዔ = ?
          7× 7= 49
30 ስንገድፈው (49÷30) =1 ደርሶ 19 ይቀራል
          19 ጥንተ መጥቅዕ ይባላል።
መጥቅዕና አበቅቴ ተደምረው 30 አይበልጡም 30 አያንሱም
አዋጅ  በቅ ወመጥቅዕ ክልዔሆሙ ኢየዓ እም፴ ይወርዱ እም፴  ወትረ ይከውኑ ”  ይላል።
ሕዝቡስ ሜጥሮስ በፊት እንዴት ያከብር ነበር?
                  
አዕዋዳት
አዕዋድ ከሚል የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ዞረ ማለት ሲሆን በየጊዜው እየዞረ የሚመጣ ማለት ነው።
ዓመተ ዓለም የሚሠርበት ሰባት አዕዋዳት አሉ። እነሱም፦
Ø  ዓውደ ዕለት - እሁድ
Ø  ዓውደ ወርኅ በፀሐይ 30 ቀናት በጨረቃ 29 30
Ø  ዓውደ ዓመት- በፀሐይ 365 ቀናት 6 ሰዓት (15 ኬክሮስ) በጨረቃ 354 22 ኬክሮስ
Ø  ዓውደ አበቅ (ንዑስ ቀመር) = 19 ዓመት
Ø  ዓውደ ፀሐይ = 28 ዓመት
Ø  ዓውደ ማኅተም (ማዕከላዊ ቀመር) = 76 ዓመት
Ø  ዓውደ ዐቢይ ቀመር (ዐቢይ ቀመር) = 562
ወንበር
·         የዘመኑን አበቅቴንና መጥቅዕ የሚያስገኝ ነው።
·         ወንበር ለማግኘት ቀድመን ዓመተ ዓለሙን ማውጣት
          5500 ዓመተ ፍዳ፣ ዓመተ ኩነኔ
          2007 ዓመተ ምህረት ዓመተ ሥጋዌ (ለምን ዓመተ ምህረት ተባለ?)
            በድምሩ 7507
ይህንና በሶስቱ ቀመሮች እንቀምረዋለን።
·         ቀመር    532
·         ከላዊ ቀመር 76
·         ንዑስ ቀመር፣    19
1. ለዐ ቀመር
          7507 ÷ 532
          14 ቀመር 7448 ሆኖ 59 ይቀራል
2. ለማከላዊ ቀመር
          59 ከላዊ ቀመር (76) አይችልም
3. ለንዑስ ቀመር
          59÷19= 3 ጊዜ ደርሶ 2 ይቀራል
አዋጅ  አሐደ አዕት ለዘመን  - አንድ ለዘመኑ ስጥ
Ø  ለምን አንድ እንቀንሳለን? /ከብሎጉ ይመልከቱ/
2 – 1 ዜሮ
2007 .. ወንበር አንድ ይሆናል::
2009 ሥራ?
Ø  ቅቴ  ከሚል የግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን
·         ተረፈ ዘመን
·         ቁጥረ ሌሊት
·         ሌሊት ማለት ነው።

Ø  አበቅቴን ለማግኘት
          ጥንተ አበቅቴ ከወንበር ጋር ማባዛት
          30 ከበለጠ - 30 መግደፍ
ቅቴ = 11 × 1 = 11 ( አስራ አንድ ይሆናል)
Ø  በ2007 ዓ.ም አስራ አንድ አበቅቴ ወጣ እንላለን።

Ø  አበቅቴ የሚጠቅመን ሌሊቱን ለማግኘት ነው።
·         ሌሊት = ዕለት + አበቅቴ + ሕፀጽ

ሕፀጽ
- ጐደለ
ሕፀ - ጉድለት ማለት ነው።
ጨረቃ ከፀሐይ የምታጐድለው ማለት ነው።
የዓመቱ ሕፀጽ፦
·         የመስከረምና የጥቅምት = 1
·         የሕዳርና ታህሣሥ= 1 ከላይኛው ጋር = 2
·         የጥርና  የካቲት =     3
·         የመጋቢትና የሚያዚያ =
·         የግንቦትና የሰኔ =       5
·         የሐምሌና የነሐሴ = 6
·         ጳጉሜ ወር ስለማትሞላ 6 ነው።
·         የመስከረም 1/2007 . ሌሊት
          ዕለት + ቅቴ + ሕፀጽ
          1 + 11 + 1 = 13
          ጳጉሜን አምስት ለመስከረም አንድ አስራ ሶስት ሌሊት ያድራል።
መጥቅዕ
·         ደወል ማለት ነው
ደወል ሲመታ የራቁ ይቀርባሉ፣ የተበተኑ ይሰበሰባሉ ይህም መጥቅዕ በዓላትና አጽዋማትን ይሰበስባል።
የዘመኑን መጥቅዕ ለማግኘት ጥንተ መጥቅዕን ከወንበር ጋር ማባዛት
·         30 ከበለጠ 30 ማካፈል ነው
19 × 1 = 19
የመጥቅዕ ጥቅም ከዕለት ተውሳክ ጋር ተደምሮ መባጃ ሐመርን ያስገኝልናል።
ሐመር
·         ባጀ - ቆየ ሰነበተ
·         ሐመርመርከብ

·         በዓላትና አጽዋማት የሚያሰነብት ስለሆነ መባጃ ሐመር ተብሏል።
መባጃ ሐመርን ለማግኘት
·         መጥቅዕና በዓለ መጥቅዕ የዋለበትን የዕለት ተውሳ መደመር ነው።
          30 ከበከጠ 30 መግደፍ
በዓለ መጥቅዕ መቼ ይውላል?
አዋጅ መጥቅዕ 14 በላይ ከሆነ በመስከረም
            14 በታች ከሆነ በጥቅምት
          (መጥቅዕ ሲበዛ ከመስከረም ንዛ መጥቅዕ ሲያንስ ጥቅምትን ዳስ እንዲሉ አበው)
            መጥቅዕ 19 ነው ( 19 > 14)
በዓለ መጥቅዕ በመስከረም (በመስከረም 19) ቀን ይውላል።
የዕለት ተውሳክ
·         ተውሳክ  -    ወሰከ - ጨመረ
-          ጭማሪ ማለት ነው።
·         የቅዳሜ ተውሳክ -  8
·         የእሑድ    -       7
·         የሰኞ       -       6
·         የማክሰኞ   -       5
·         የረቡዕ     -       4
·         ሐሙስ     -       3
·         ዓርብ      -       2
መስከረም 19/2007 . . ሰኞ ይውላል (6 ተውሳክ)
ባጃ ሐመር = መጥቅዕ + የዕለት ተውሳክ
                       19 + 6 = 25
የመባጃ ሐመር ጥቅም
ከበዓላትና አጽዋማት ተውሳክ ጋር በመደመር የየዘመኑንን በዓላትንና አጽዋማት ያስገኝልናል።

የበዓላትና አጽዋማት ተውሳክ
          1. ጾመ ነነዌ  ተውሳክ የላትም (0 ነው)
                 ስለዚህ መባጃ ሐመር ብቻውን ይመራታል
አዋጅ በዓለ መጥቅዕ በመስከረም ከዋለ ጾመ ነነዌ በጥር ትገባለች
           በዓለ መጥቅዕ በጥቅምት ከዋለ ጾመ ነነዌ በየካቲት ትገባለች
            በዓለ መጥቅዕ በመስከረም 30 ከዋለ በጥቅምት ትገባለች
       2. የዐቢይ ጾም ተውሳክ   = 14
       3. የበዓለ ደብረ ዘይት     = 11
       4. የበዓለ ሆሳዕና         = 2
       5. የበዓለ ስቅለት         = 7
       6. የበዓለ ትንሣኤ        = 9
       7. የበዓለ ርክበ ካህናት    = 3
       8. የበዓለ ዕርገት          = 18
       9. የበዓለ ጰራቅሉጦስ      = 28
       10. ጾመ ሐዋርያት         = 29
       11. ጾመ ድኅነት            = 1
                   በዓላትና አጽዋማት
1.   ጾመ ነነዌ ተውሳክ የላትም ስለዚህ በመባጃ ሐመር ብቻ ትመራለች። መባጃ ሐመር 25 ስለሆነ እንዲሁም በዓለ መጥቅዕ በመስከረም ስለዋለ ጾመ ነነዌ ጥር 25 ትገባለች።
  25 + 0 = 25  ጥር 25
2.   በዐተ ዐቢይ ጾም 25 + 14 = 39 (በ30 ስንገድፈው 9 ይቀራል)
                    የካቲት = 9
3.   ደብረ ዘይት  25 + 11 = 36 (በ30 ስንገድፈው 6 ይቀራል)
                   መጋቢት 6
4.   በዓለ ሆሳዕና  25 + 2 = 27
መጋቢት 27 5 ()
5.   በዓለ ስቅለት 25 + 7 = 32 (በ30 ስንገድፈው 2 ይቀራል)
                  ሚያዚያ 2 ( ርብ)
6.   በዓለ ትንሣኤ 25 + 9 = 34 (በ30 ስንገድፈው 4 ይቀራል)
                   ሚያዚያ 4 ()
7.   በዓለ ርክበ ካህናት 25 + 3 = 28
ሚያዚያ 28 (ረቡዕ)
8.   በዓለ ዕርገት 25 + 18 = 43 (በ30 ስንገድፈው 13 ይቀራል)
                 ግንቦት 13 (ሐሙስ)
9.   በዓለ ጰራቅጦስ  25 + 28 = 53
                   30 ሲገደፍ 23 ይቀራል
                   ግንቦት 23 ()
10.               ጾመ ሐዋርያት 25 + 29 = 54 (ነ30 ስንገድፈው 24 ይቀራል)
                        ግንቦት 24 (ሰኞ)
11.               ጾመ ድኅነት   25 + 1 = 26
ግንቦት  26 (ረቡዕ)
ኢየዓርግና አይወርድ
·  ጾመ ነነዌ ከጥር 17 አትወርድም ከየካቲት 21 አትወጣም



የተረሱ ወይም ወደፊት የምንፈልጋቸውን ቀናትን ማግኘት
       ለምሳሌ 2007 በዓለ መጥቅዕን ለማግኘት ብንፈልግ
       መስከረም 19/2007
·  ወንጌላውያኑን ማግኘት
       ዓመተ ፍዳ + . .
       5500 + 2007 = 7507
ዓመተ ዓለሙን 4 ወንጌላውያን በማካፈል
·         ቀሪው 1 ከሆነ    ማቴዎስ
·         2 ከሆነ           ማርቆስ
·         3 ከሆነ           ሉቃስ
·         4 ከሆነ           ዮሐንስ
7507 ÷ 4 = 1876 ደርሶ 3 ይቀራል
          ንጌላዊው  ሉቃ
2. መስከረም 1 ( ዕለተ ቀመር)
          ዓመተ ዓለም + መጠነ ራብዒት = ለሰባቱ ዕለታት ማካፈል
            7507 + 1876 = 9383
            9383 ÷ 7= 1340 ደርሶ 3 ይቀራል ቀሪ
·         1 ከሆነ = ማክሰኞ
·         2 ከሆነ = ረቡዕ
·         3 ከሆነ = ሐሙስ
·         4 ከሆነዓርብ
·         5 ከሆነ = ቅዳሜ
·         6 ከሆነ = እሁድ
·         0 ከሆነሰኞ
3 . ዕለቱን ለማግኘት፦ ሶስት ነገሮች ይደመራሉ
       ዕለት + አጽፈ ወርኅ + ጥንተ
       መስከረም 19 + የመስከረም እጥፍ + ጥንተ ዮን
ጥንተ ዮን መስከረም 1 ረቡዕ ከዋለ = ጥንተ ዮን አንድ ነው።
·         ሐሙስ ከዋለ   = 2
·         ዓርብ ከዋለ    = 3
·         ቅዳሜ ከዋለ   = 4
·         እሑድ ከዋለ   = 6
·         ሰኞ ከዋለ      = 7
·  መስከረም 1 ቀን ሐሙስ ስለዋለ ጥንተ ዮን ሁለት ነው።
             ዕለት + አጽፈ ወርኅ + ጥንተ ዮን
              19 + 2 + 2 = 23
23ን ለሰባት ማካፈልና ቀሪው
·  1 ከሆነ    እሁድ
·  2 ከሆነ    ሰኞ
·  3 ከሆነ    ማክሰኞ
·  4ከሆነ     ረቡዕ
·  5 ከሆነ     ሐሙስ
·  6 ከሆነ    ዓርብ
·  0 ከሆነ     ቅዳሜ
                   23 ÷ 7= 3  ጊዜ ደርሶ 2 ይቀራል
                   መስከረም 19  ሰኞ ይውላል
       የቤት ስራ
1.  የአድዋ ድል መቼ ነበር ?
2. ጌታ የተጠመቀበት መቼ ነበር?
3. የ2010ን በዓለ ትንሳኤንና በዓለ ርክበ ካህናትን አውጣ!





No comments:

Post a Comment

Thank you for your comments, we will response on timely manner.
thank you again.