Thursday, September 11, 2014

እንኳን ለ፳፻፯ /2007/ ዓመተ ምህረት ዘመነ
     ሉቃስ በሰላም በጤና አደረስዎ!


ባሕረ ሐሳብ
Ø  ባሕረ ሐሳብ ከሁለት የግዕዝ ላት የተገኘ ሲሆን
ባሕር  =  ዘመን
ሀሳብ  =  ቁጥር ማለት ነው። /ዝርዝሩን ከብሎጉ ይመልከቱ/
ባሕረ ሐሳብ ማን ደረሰው ?
Ø  የእስክንድርያ 12 ሊቀ ጳጳስ (ፓትርያርክ) የነበረው ቅዱስ ሜጥሮስ
180 – 222 . ድረስ 42 ዓመት ሊቀ ጳጳስ ነበር። ሊቀጳጳስ ከመሆኑ በፊት መስተገብረ ምድር (ገበሬ) ነበር። አርቆ በአጭር ታጥቆ የሚሰራ ትጉህ ገበሬ ነበር። ከልዕልተ ወይን (የቤተክርስቲያን ለቃውንት የሚጠሯት ስም) ጋር አጋብተዋቸው ነበር። /ሙሉ ታሪኩን ብሎጉን ይጎብኙ/
የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ ዩልዩስ (ዩልያኖስ) ሹሞታል።  
ባሕረ ሐሳብ በመጽሐፍት ቤት
Ø  ቤተ ክርስቲያን አራት ጉባዔ ቤቶች አሏት
·         ብሉይ ኪዳን
·         ሐዲስ ኪዳን
·         መጽሐፈ መነኮሳት (ማር ይስሐቅ፣ ፈልክ)
·         ሊቃውንት (ሃይማኖተ አበው)
·         አምስተኛ ጉባዔ  ተደርጐ በሁለት መንገድ ይሰጣል። አቡክር (አቡኻር) ባሕረ ሀሳብ ተብሎ
Ø  አቡኻር (ወልደ አቤል ሄሬም) የተባለ መነኩሴ ሲሆን ባሕረ ሐሳብን ጨምሮ ሌሎች የሥነ ጸሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት ሊቅ ነው። ባሕረ ሀሳብም አብሮ ተገልጾለታል።

Ø

Tuesday, September 10, 2013

ባሕረ ሐሳብ

እንኳን ለ፳፻፮ /2006/ ዓመተ ምህረት ዘመነ
ማርቆስ በሰላም በጤና አደረስዎ!

Ø  ባሕረ ሐሳብ ከሁለት የግዕዝ ላት የተገኘ ሲሆን
ባሕር  =  ዘመን
ሀሳብ  =  ቁጥር ማለት ነው። /ዝርዝሩን ከብሎጉ ይመልከቱ/ 

ባሕረ ሐሳብ ማን ደረሰው ?
Ø  የእስክንድርያ 12 ሊቀ ጳጳስ (ፓትርያርክ) የነበረው ቅዱስ ሜጥሮስ
180 – 222 . ድረስ 42 ዓመት ሊቀ ጳጳስ ነበር። ሊቀጳጳስ ከመሆኑ በፊት መስተገብረ ምድር (ገበሬ) ነበር። አርቆ በአጭር ታጥቆ የሚሰራ ትጉህ ገበሬ ነበር። ከልዕልተ ወይን (የቤተክርስቲያን ለቃውንት የሚጠሯት ስም) ጋር አጋብተዋቸው ነበር።
የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ ዩልዩስ (ዩልያኖስ) ሹሞታል።  /ሙሉ ታሪኩን ብሎጉን ይጎብኙ/

ባሕረ ሐሳብ በመጽሐፍት ቤት
Ø  ቤተ ክርስቲያን አራት ጉባዔ ቤቶች አሏት
·         ብሉይ ኪዳን
·         ሐዲስ ኪዳን
·         መጽሐፈ መነኮሳት (ማር ይስሐቅ፣ ፈልክዲዳዩስ)
·         ሊቃውንት (ሃይማኖተ አበው)
·         አምስተኛ ጉባዔ  ተደርጐ በሁለት መንገድ ይሰጣል። አቡከክር (አቡካኻር) ባሕረ ሀሳብ ተብሎ
Ø  አቡካኻር (ወልደ አቤል ሄሬም) የተባለ መነኩሴ ሲሆን ባሕረ ሐሳብን ጨምሮ ሌሎች የሥነ ጸሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት ሊቅ ነው። ባሕረ ሀሳብም አብሮ ተገልጾለታል።

Saturday, January 12, 2013

ወንበር

በዓላትንና አጽዋማትን ለማውጣት ከሚያስፈልጉን ነገሮች ውስጥ አንዱ መጥቅዕ ሲሆን በዓላትና አጽዋማት የሚያድሩባቸውን ሌሊት የሚያሳውቀን ደግሞ አበቅቴ ነው። አበቅቴና መጥቅዕ በየዘመኑ የሚቀያየሩ ስለሆነ ሁልጊዜ ማለትም በየዓመቱ የየዘመኑን አበቅቴና መጥቅዕ ማውጣት ይኖርብናል። እንግዲህ ወንበር እነዚህን አበቅቴንና መጥቅዕን የምናወጣበት ቁጥር ነው። ወንበር የሚለው ስያሜ የተገኘው አበቅቴም ሆነ መጥቅዕ /ለበዓላትና ለአጽዋማት መገኘት ወሳኙ የሆኑ ነገሮች/ የሚገኝበት ከመሆኑም በላይ ዓመቱን ሙሉ ቀሚ በመሆን የሚያገለግል ቁጥር ስለሆነ ነው።

ወንበር እንዴት ይወጣል?
ወንበርን በተለያየ መንገድ ማውጣት የምንችል ሲሆን ሊቃውንት አባቶቻችን እንደ ዛሬው የሂሳብ መቀመሪያ መሳሪያዎች ሳይኖሩ የሂሳብ ስሌቶችን የሚሰሩት በቃላቸው ነበር። አሁንም አብዛኛዎቹ በቃላቸው ነው የሚሰሩት። ለምሳሌ አንድን ትልቅ ቁጥር ለሆነ ቁጥር ማካፈል ቢፈልጉ /ለምሳሌ 7450ን ለ532 ለማካፈል/ የሚጠቀሙት እንደኛ ካልኩሌተር ሳይሆን በቃላቸው ነው የሚያካፍሉት። በዚህን ጊዜ ይንን ትልቅ ቁጥር ለማካፈል የተለያዩ መንገዶችነ ይጠቀማሉ። ስለዚህ ይህንን የአባቶችን ትውፊት መተው ተገቢ ስላልሆነ እንዲሁም አንዱም መንገድ በመሆኑ እንመለከተዋለን። ሌላው ደግሞ ዘመኑ የሰጠንን አጭር መንገዶችንም መጠቀሙ ለስራችን ቅልጥፍና የሚሰጠው በመሆኑ በዘመናዊ መንገድ በማለት እንመለከተዋለን።Monday, December 31, 2012

አዕዋዳት

አዕዋዳት የሚለው ዖደ ከሚለው ግስ የተገኘ ሲሆን ዞረ ማለት ነው። አዕዋዳት ደግሞ በብዙ እየዞረ የሚመጣ ማለት ነው። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ጥንት ከሚለው እንደሚጀምር አይተናል። ጥንትነቱም ከፍጥረተ ዓለም፣ ከፍጥረተ ፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት ነው። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ሳድሲቱ ዐምሲት፣ ዐምሲቱ ራብዒት፣ ራብዒቱ ሳልሲት፣ ሳልሲቲ ካልዒት፣ ካልዒቱ ኬክሮስ፣ ኬክሮሱ ሰዓታት፣ ሰዓታቱ ሳምንታት፣ ሳምንታቱ  ወራት፣ ወራቱ ዓመታት፣ ዓመታቱ አዝማናት እየሆኑ ዛሬ ካለንበት ላይ ደርሰል። ሳድሲት፣ ዐምሲት፣ ራብኢት … ወዘተ ተብለው የተገለጹት በዘመናዊው አነጋገር ማይክሮ ሰከንድ፣ ሚኒ ሰከንስ፣ ሰከንድ … ወዘተ እንንደሚባሉት እጅግ በጣም ደቃቅ የሆኑ የጊዜ መለኪያዎች ናቸው። ጊዜያቸው ወይም ቆይታቸው ከዓይን ቅጽበት ያነሰ በመሆኑ አንጠቀምባቸውም፤ በዚህም ምክንያት የተለመዱ አይደሉም። ዓለምከተፈጠረ ዘመን ከተቆጠረ በፀሐይ 5005 ዓመተ ዓለም ነው። ይኸውም


Wednesday, October 3, 2012

የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ከየት ይጀምራል?


የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሚጀምረው ከፍጥረተ ዓለም፣ ከፍጥረተ ጸሐይ፣ ከፍጥረተ ጨረቃ ጋር የተያያዘ ሲሆን የሚጀምረውም ጥንት ከሚለው ነው። ጥንትነቱም ከእነዚሁ ከዓለም፣ ከጸሀይ ፣ ከጨረቃና ከዋክብት መፈጠር ጋር የተያያዘ ሲሆን በጸሐይ ሶስት  ጥንታት አሉ። እነሱም፦-

1.      ጥንተ ዕለት፦ ጥንተ ዕለት እሑድ ሲሆን በዚህ ቀን ዓለም ማለትም ሰማይና ምድር የተፈጠረበት ቀን ነው።

2.     ጥንተ ቀመር፦ ይህ ዕለት ሠሉስ /ማክሰኞ/ ሲሆን በዚህ ቀን በዓለም ውስጥ የሚገኙ ፍጥረታት /ዕፅዋት፣ አዝርዕት፣ አታክልት/ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጠሩበት ቀን ነው።

3.     ጥንተ ዮን፦ ጥንተ ዮን ዕለተ ረቡዕ ሲሆን በዚህም የቀንና የሌሊት መክፈያ የሆኑት ጸሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት የተፈጠሩበት ቀን ነው። ዮን ማለት ጸሐይ ማለት ነው። “ዮን ይዕቲ ስማ ለጸሐይ ሀገረ ጸሐይ ዮን ይዕቲ” እንዲል።

እንግዲህ የኢትዮጵያ ዘመን መቆጠር የጀመረው ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ነው። ስለ ዘመን ቆጠራም ስንናገር “ዓለም ከተፈጠረ ዘመን ከተቆጠረ” እንላለን። ስለዚህ ዘመን ቆጠራችን ከሥነ ፍጥረት ጋር የተያያዘ ነው።

Wednesday, September 26, 2012


ቅድመ ድሜጥሮስ ሕዝቡ በዓላትን እንዴት ያከብር ነበር?

እግዚአብሔር እምቅድመ ዓለም በልብ የመከረውን በነቢያት ያናገረውን ለመፈጸም በሥጋ ሰብዕ ተገልጿል/። በሥጋ ሰብዕም ተገልጾ ሕግ መጽሐፋዊ እና ሕግ ጠባይዓዊ ሲፈጽም አደገ። ሕግ መጽሐፋዊ ማለት በኦሪት እና በነቢያት ስለእርሱ የተጻፉትን እና የተነገሩትን መፈጸም ሲሆን ለምሳሌ።

·         በስምንት ቀን ቤተ ግዝረት ገብቶ መገዘር፣

·         በዐርባ ቀን ዕጉለ ርግብ ዘውገ መዕነቅ ይዞ ቤተ መቅደስ መግባት፣

·         በዓመት ሶስት ጊዜ ለገቢረ በዓል መውጣት “ለያስተርኢ ተባዕትከ ሠለስተ ጊዜያተ ለለዓመት” እንዲል፣

ሕግ ጠባይዓዊ ማለት በአንድ ሥጋ በለበሰ ሰው የሚንጸባረቁ ባሕርያት ሲሆኑ ለምሳሌ፦

·         በየጥቂቱ ማደግ “በበሕቅ ልሕቀ - በየጥቂቱ አደገ”

·         ለእናቱና ለቤተሰቦቹ መታዘዝ “እንዘ ይትኤዘዝ ለአዝማዲሁ- ለቤተሰቦቹ እየታዘዘ አደገ” እንዲል።

Wednesday, September 19, 2012


ባሕረ ሐሳብን ማን ደረሰው?

ባሕረ ሐሳብን ለማወቅ ብዙ አባቶች ተመኝተው ነበር። ይሁን እንጂ ሁሉ የሚሆነው በእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና የመንበረ እስክንድርያ አስራ ሁለተኛ ሊቀ ጳጳስ ለነበረው ለቅዱስ ድሜጥሮስ ተጸልጾለታል። ድሜጥሮስ ማለት መስታወት ማለት ነው። መስታወት፦ በጥርስ ያለውን እድፍ በጸጉር ያለውን ጉድፍ እንደሚያሳይ ሁሉ ድሜጥሮስም የተሰወሩ በዓላትን እና አጽዋማትን አሳይቶናል፤ አንድም ድሜጥሮስ ማለት መነጽር ማለት ነው። መነጽር፦ የራቀውን አቅርቦ የረቀቀውን አጉልቶ የተበተነውን ሰብስቦ እንደሚያሳየው ሁሉ ድሜጥሮስም የራቁ አዝማናትን አቅርቦ የተበተኑ አጽዋማትን ሰብስቧልና  መስታወት ተብሏል።

                                                ቅዱስ ድሜጥሮስ