እንኳን ለ፳፻፮ /2006/
ዓመተ ምህረት ዘመነ
ማርቆስ በሰላም በጤና አደረስዎ!
Ø ባሕረ ሐሳብ ከሁለት የግዕዝ ቃላት የተገኘ ሲሆን
ባሕር = ዘመን
ሀሳብ = ቁጥር ማለት ነው። /ዝርዝሩን ከብሎጉ ይመልከቱ/
ባሕረ
ሐሳብ ማን ደረሰው ?
Ø የእስክንድርያ 12ኛ ሊቀ ጳጳስ (ፓትርያርክ) የነበረው ቅዱስ ድሜጥሮስ
ከ
180 – 222 ዓ.ም ድረስ ለ 42 ዓመት ሊቀ ጳጳስ ነበር። ሊቀጳጳስ ከመሆኑ በፊት መስተገብረ ምድር (ገበሬ) ነበር።ዲኮ አርቆ፣ በአጭር ታጥቆ የሚሰራ ትጉህ ገበሬ ነበር። ከልዕልተ ወይን (የቤተክርስቲያን ለቃውንት የሚጠሯት ስም) ጋር አጋብተዋቸው ነበር።
የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ ዩልዩስ (ዩልያኖስ) ሹሞታል። /ሙሉ ታሪኩን
ብሎጉን ይጎብኙ/
ባሕረ
ሐሳብ በመጽሐፍት ቤት
Ø ቤተ ክርስቲያን አራት ጉባዔ ቤቶች አሏት
·
ብሉይ ኪዳን
·
ሐዲስ ኪዳን
·
መጽሐፈ መነኮሳት (ማር ይስሐቅ፣ ፈልክዲዳዩስ)
·
ሊቃውንት (ሃይማኖተ አበው)
·
አምስተኛ ጉባዔ ተደርጐ በሁለት መንገድ ይሰጣል። አቡከክር
(አቡካኻር)
ባሕረ ሀሳብ ተብሎ
Ø አቡካኻር (ወልደ አቤል ሄሬም) የተባለ መነኩሴ ሲሆን ባሕረ ሐሳብን ጨምሮ ሌሎች የሥነ ጸሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት ሊቅ ነው። ባሕረ ሀሳብም አብሮ ተገልጾለታል።
Ø ከዲሜጥሮስ በተጨማሪ ባሕረ ሀሳብን ለማወቅ የተመኙ
1.
ሰዒድ ወልደ ጰጥሪቅ
2.
መሀቡብ ወልደ መንጋ
3.
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
4.
ኤጲፋንዮስ ዘመንፈስ ቅዱስ
5.
ጊዮርጊስ ወልደ አሚድ
6.
ማርቆስ ወልደ ቀምበር
7.
ዮሐንስ ወርልደ አቤልሔሬም (አቡካክር) … እና ሌሎችም
የቅዱስ ድሜጥሮስ
ምኞት
Ø
በዓላትና አጽዋማት ከጥንተ ዕለታቸው ባይጡ ባይነዋወጡ እያለ ይመኝ ነበር። ይኸውም
·
ጾመ ነነዌ፣ ዐብይ ጾም፣ ጾመ ሐዋርያት፣ ከሰኞ፣
·
በዓለ ርክበ ካህናት፣ ጾመ ድኅነት ከረቡዕ፣
·
በዓለ ዕርገት ከሐሙስ፣
·
በዓለ ደብረ ዘይት፣ ሆሳዕና፣ ትንሳኤ፣ ጰራቅሊጦስ ከእሁድ
Ø
መልአከ እግዚአብሔር ነገረ በምኛት አይሆንም ሱባዔ ገብተህ አግኘው አለው
ከሌሊቱ 23 ሱባዔ ገብተህ አበቅቴ፣
አቀኑ 7 ሱባዔ መጥቅዕ ይሁንህ ብሎታል
ምነው ሌሊቱን አብዝቶ ቀኑን አሳነሰው?
/ ከብሎጉ ይመልከቱ/
23 ሱባዔ ማለት
1 ሱባዔ = 7 ቀናት
23 ሱባዔ = ?
161 ቀናት
አዋጅ ፦ ማንኛውም ቁጥር ከ30 በ30 ግደፈው
161
÷ 30 = 5 ደርሶ 11 ይቀራል
11 ጥንተ አበቅቴ ይባላል።
ሰባት ሱባዔ ማለት፦
1 ሱባዔ = 7
7 ሱባዔ = ?
7× 7= 49
በ 30 ስንገድፈው (49÷30) =1 ደርሶ
19 ይቀራል
19 ጥንተ መጥቅዕ ይባላል።
መጥቅዕና አበቅቴ ተደምረው ከ 30 አይበልጡም ፣ ከ 30 አያንሱም
አዋጅ “አበቅቴ ወመጥቅዕ ክልዔሆሙ ኢየዓርጉ እም፴ ወኢይወርዱ እም፴ ወትረ ይከውኑ ፴” ይላል።
ሕዝቡስ ከድሜጥሮስ በፊት እንዴት ያከብር ነበር?
አዕዋዳት
አዕዋድ ዖደ ከሚል የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ዞረ ማለት
ሲሆን በየጊዜው እየዞረ የሚመጣ ማለት ነው።
ዓመተ ዓለም የሚሠፈርበት ሰባት አዕዋዳት አሉ። እነሱም፦
Ø
ዓውደ ዕለት ከሰኞ
- እሁድ
Ø
ዓውደ ወርኅ በፀሐይ 30 ቀናት፤ በጨረቃ 29ና 30
Ø
ዓውደ ዓመት- በፀሐይ 365 ቀናት 6 ሰዓት (15 ኬክሮስ)፤ በጨረቃ
354 ከ 22 ኬክሮስ
Ø
ዓውደ አበቅቴ
(ንዑስ ቀመር) = 19 ዓመት
Ø
ዓውደ ፀሐይ = 28 ዓመት
Ø
ዓውደ ማኅተም (ማዕከላዊ ቀመር) = 76 ዓመት
Ø
ዓውደ ዐቢይ ቀመር (ዐቢይ ቀመር) = 562
ወንበር
·
የዘመኑን አበቅቴንና መጥቅዕ የሚያስገኝ ነው።
·
ወንበር ለማግኘት ቀድመን ዓመተ ዓለሙን ማውጣት
5500 ዓመተ ፍዳ፣ ዓመተ ኩነኔ
2006 ዓመተ ምህረት ዓመተ ሥጋዌ (ለምን ዓመተ ምህረት ተባለ?)
በድምሩ 7506
ይህንና በሶስቱ ቀመሮች እንቀምረዋለን።
·
ዐቢይ ቀመር ፣ 532
·
ማዕከላዊ ቀመር ፣76
·
ንዑስ ቀመር፣ 19
1ኛ.
ለዐቢይ ቀመር
7506 ÷ 532
14ቱ ዐቢይ ቀመር 7448 ሆኖ 58 ይቀራል
2ኛ.
ለማዕከላዊ ቀመር
58 ማዕከላዊ ቀመር (76)
አይችልም
3ኛ.
ለንዑስ ቀመር
58÷19= 3 ጊዜ ደርሶ 1 ይቀራል
አዋጅ “አሐደ አዕትት ለዘመን - አንድ ለዘመኑ ስጥ”
Ø
ለምን አንድ እንቀንሳለን? /ከብሎጉ ይመልከቱ/
1 -- 1 ዜሮ
የ 2006 ዓ.ም. ወንበር ዜሮ ይሆናል
2009ን ሥራ?
አበቅቴ
Ø
አበቅቴ አፖክቴ ከሚል የግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን
·
ተረፈ ዘመን
·
ቁጥረ ሌሊት
·
ሥፍረ ሌሊት ማለት ነው።
Ø
አበቅቴን ለማግኘት፦
ጥንተ አበቅቴ ከወንበር ጋር ማባዛት
ከ30 ከበለጠ - በ30 መግደፍ
አበቅቴ =
11 × 0 =
0 ( አልቦ አበቅቴ ይሆናል)
Ø
ይህ ማለት ፀሐይና ጨረቃ በተፈጠሩበት መስኮት ተገናኝተዋል ማለት ነው።
Ø
አበቅቴ የሚጠቅመን ሌሊቱን ለማግኘት ነው።
·
ሌሊት = ዕለት +
አበቅቴ +
ሕፀጽ
ሕፀጽ
ሐፀ - ጐደለ
ሕፀጽ - ጉድለት ማለት ነው።
ጨረቃ ከፀሐይ የምታጐድለው ማለት ነው።
የዓመቱ ሕፀጽ፦
·
የመስከረምና የጥቅምት = 1
·
የሕዳርና ጠታህሣሥ= 1 ከላይኛው ጋር = 2
·
የጥርና ጠየካቲት = 3
·
የመጋቢትና የሚያዚያ =
·
የግንቦትና የሰኔ = 5
·
የሐምሌና የነሐሴ = 6
·
ጳጉሜ ወር ስለማትሞላ 6 ነው።
·
የመስከረም 1/2006 ዓ. ም ሌሊት፦ቸቸ
ዕለት + አበቅቴ
+ ሕፀጽ
1
+ 0 + 1 = 2
ጳጉሜ አምስት ማታ በተራክቦ አድረዋል።
መጥቅዕ
·
ደወል ማለት ነው
ደወል ሲመታ የራቁ ይቀርባሉ፣ የተበተኑ ይሰበሰባሉ። ይህም መጥቅዕ በዓላትና አጽዋማትን ይሰበስባል።
የዘመኑን መጥቅዕ ለማግኘት ጥንተ መጥቅዕን ከወንበር ጋር ማባዛት
·
ከ 30 ከበለጠ ለ 30 ማካፈል ነው
19
× 0 = 0
ነገር ግን አበቅቴው = 0 ስለሆነ በአዋጃችን (ወትረ ይከውኑ 30) ስለሚል የዚህ ዓመት መጥቅዕ 30 ይሆናል።
በሌላ ቋንቋ አበቅቴው ዜሮ ከሆነ ሁልጊዜም መጥቅዕ 30 ነው።
መባጃ ሐመር
·
ባጀ - ቆየ ፣ ሰነበተ
·
ሐመር - መርከብ
በዓላትና አጽዋማት የሚያሰነብት ስለሆነ መባጃ ሐመር ተብሏል።
መባጃ ሐመርን ለማግኘት፦
·
መጥቅዕና በዓለ መጥቅዕ የዋለበትን የዕለት ተውሳክ መደመር ነው።
ከ 30 ከበከጠ በ 30 መግደፍ
በዓለ መጥቅዕ መቼ ይውላል?
አዋጅ ፦ መጥቅዕ ከ14 በላይ ከሆነ በመስከረም
ከ 14 በታች ከሆነ በጥቅምት
(መጥቅዕ ሲበዛ ከመስከረም ንዛመጥቅዕ ሲያንስ ጥቅምትን ዳስ)
መጥቅዕ 30 ነው ( 30 >
14)
በዓለ መጥቅዕ በመስከረም (በመስከረም 30) ቀን ይውላል።
የዕለት ተውሳክ፦
·
ተውሳክ - ወሰከ
- ጨመረ
-
ጭማሪ ማለት ነው።
·
የቅዳሜ ተውሳክ - 8
·
የእሑድ - 7
·
የሰኞ - 6
·
የማክሰኞ - 5
·
የረቡዕ - 4
·
ሐሙስ - 3
·
ዓርብ - 2
መስከረም
30/2006 ዓ. ም. ሐሙስ ይውላል (3 ተውሳክ)
መባጃ ሐመር = መጥቅዕ + የዕለት ተውሳክ
30 + 3 = 33
በ 30 ሲገደፍ = 3
የመባጃ ሐመር ጥቅም
ከበዓላትና አጽዋማት ተውሳክ ጋር በመደመር የየዘመኑንን በዓላትንና አጽዋማት ያስገኝልናል።
የበዓላትና
አጽዋማት ተውሳክ የሚውልበት
1ኛ. ጾመ
ነነዌ ተውሳክ
የላትም (0 ነው)
ስለዚህ
መባጃ ሐመር ብቻውን
ይመራታል
አዋጅ ፦ በዓለ
መጥቅዕ በመስከረም ከዋለ
ጾመ ነነዌ በጥር
ትገባለች፣
በዓለ
መጥቅዕ በጥቅምት ከዋለ
ጾመ ነነዌ በየካቲት
ትገባለች
በዓለ
መጥቅዕ በመስከረም 30 ከዋለ
በጥቅምት ትገባለች
ዘንድሮ
አልቦ አበቅቴ ሆኖ
በመስከረም 30 በዓለ መጥቅዕ
ስለዋለ ጾመ ነነዌ በየካቲት ትገባለች።
2ኛ. የዐቢይ ጾም
ተውሳክ = 14
3ኛ. የበዓለ ደብረ
ዘይት =
11
4ኛ. የበዓለ ሆሳዕና =
2
5ኛ. የበዓለ ስቅለት =
7
6ኛ. የበዓለ ትንሣኤ =
9
7ኛ. የበዓለ ርክበ
ካህናት =
3
8ኛ. የበዓለ ዕርገት = 18
9ኛ. የበዓለ ጰራቅሉጦስ = 28
10ኛ. ጾመ ሐዋርያት = 29
11ኛ. ጾመ ድኅነት = 1
በዓላትና አጽዋማት
1.
ጾመ ነነዌ
መባጃ ሐመር ተውሳክ የላትም
3 + 0 = 3 የካቲት
3
2.
በዐተ ዐቢይ
ጾም 3 + 14 = 17
የካቲት
= 17
3.
ደብረ ዘይት 3 + 11 = 14
መጋቢት
14
4.
በዓለ ሆሳዕና 3 + 2 = 5
ሚያዚያ
5 (እሁድ)
5.
በዓለ ስቅለት
3 +
7
= 10
ሚያዚያ
10 ( አርብ)
6.
በዓለ ትንሣኤ
3 +
9
= 12
ሚያዚያ
12 (እሁድ)
7.
በዓለ ርክበ
ካህናት 3 + 3 = 6
ግንቦት 6
8.
በዓለ ዕርገት
3 + 18 = 21
ግንቦት
21 (ሐሙስ)
9.
በዓለ ጰራቅሊጦስ 3 + 28 = 31
በ
30 ሲገደፍ 1 ይቀራል
ሰኔ
1 (እሁድ)
10.
ጾመ ሐዋርያት
3 +
29
=
32
ሰኔ
2 (ሰኞ)
11.
ጾመ ድኅነት 3 + 1 = 4
ሰኔ
4 (ረቡዕ)
ኢየዓርግና
አይወርድ
· ጾመ
ነነዌ ከጥር 17 አትወርድም
ከየካቲት 21 አትወጣም
የተረሱ
ወይም ወደፊት የምንፈልጋቸውን ቀናትን
ማግኘት
ለምሳሌ
የ 2006 በዓለ መጥቅዕን
ለማግኘት ብንፈልግ
መስከረም
30/2006
·
1. 1. ወንጌላውያኑን ማግኘት
ዓመተ
ፍዳ + ዓ. ም.
5500
+
2006
= 7506
ዓመተ
ዓለሙን ለ 4ቱ
ወንጌላውያን በማካፈል
·
ቀሪው 1 ከሆነ ማቴዎስ
·
2 ከሆነ ማርቆስ
·
3 ከሆነ ሉቃስ
· 0 ከሆነ ዮሐንስ
7506 ÷ 4 = 1876 ደርሶ 2 ይቀራል
ወንጌላዊው ማርቆስ
2. መስከረም
1 ( ዕለተ ቀመር)
ዓመተ
ዓለም + መጠነ ራብዒት
= ለሰባቱ ዕለታት ማካፈል
7506 + 1876 = 9382
9382 ÷ 7= 1340 ደርሶ
2 ይቀራል።
ቀሪ፦
·
1
ከሆነ = ማክሰኞ
·
3
ከሆነ = ሐሙስ
·
4
ከሆነ= ዓርብ
·
5
ከሆነ = ቅዳሜ
·
6
ከሆነ = እሁድ
·
0
ከሆነ = ሰኞ
3 . ዕለቱን
ለማግኘት
ዕለት
+ አጽፈ ወርኅ + ጥንተ ዮን
መስከረም
30 + የመስከረም እጥፍ + ጥንተ ዮን
ጥንተ
ዮን መስከረም 1 ረቡዕ
ከዋለ = ጥንተ ዮን
አንድ ነው።
·
ሐሙስ ከዋለ = 2
·
ዓርብ ከዋለ = 3
·
ቅዳሜ ከዋለ = 4
·
እሑድ ከዋለ = 6
·
ሰኞ ከዋለ = 7
· መስከረም
1 ቀን ረቡዕ ስለዋለ
ጥንተ ዮን አንድ
ነው።
ዕለት
+ አጽፈ ወርኅ + ጥንተ
ዮን
30 + 2 + 1 = 33
33ን ለሰባት
ማካፈልና ቀሪው
·
1
ከሆነ እሁድ
· 2 ከሆነ ሰኞ
· 3 ከሆነ ማክሰኞ
· 4ከሆነ ረቡዕ
· 5
ከሆነ ሐሙስ
· 6 ከሆነ ዓርብ
· 0 ከሆነ ቅዳሜ
33
÷ 7= 4 ጊዜ
ደርሶ 5 ይቀራል
መስከረም
30 ሐሙስ ይውላል
የቤት
ስራ
1.
የአድዋ ድል መቼ ነበር ?
2.
ጌታ የተጠመቀበት መቼ ነበር?
3.
የ2010ን በዓለ ትንሳኤንና በዓለ ርክበ ካህናትን አውጣ!
በቀጣይ አንደተለመደው ካቆምንበት
እንቀጥላለን። የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን!
አድሜና ጸጋውን አሙሉቶ አስፍቶ ይስጥልን። ይበርቱ
ReplyDeletebedend altebraram bizu example binor tiru new
ReplyDeleteegziabher yistilen