ቅድመ ድሜጥሮስ ሕዝቡ በዓላትን እንዴት ያከብር ነበር?
እግዚአብሔር እምቅድመ ዓለም በልብ
የመከረውን በነቢያት ያናገረውን ለመፈጸም በሥጋ ሰብዕ ተገልጿል/። በሥጋ ሰብዕም ተገልጾ ሕግ መጽሐፋዊ እና ሕግ ጠባይዓዊ ሲፈጽም
አደገ። ሕግ መጽሐፋዊ ማለት በኦሪት እና በነቢያት ስለእርሱ የተጻፉትን እና የተነገሩትን መፈጸም ሲሆን ለምሳሌ።
·
በስምንት ቀን ቤተ ግዝረት ገብቶ መገዘር፣
·
በዐርባ ቀን ዕጉለ ርግብ ዘውገ መዕነቅ ይዞ ቤተ መቅደስ መግባት፣
·
በዓመት ሶስት ጊዜ ለገቢረ በዓል መውጣት “ለያስተርኢ ተባዕትከ ሠለስተ ጊዜያተ ለለዓመት” እንዲል፣
ሕግ ጠባይዓዊ ማለት በአንድ ሥጋ በለበሰ ሰው የሚንጸባረቁ ባሕርያት ሲሆኑ ለምሳሌ፦
·
በየጥቂቱ ማደግ “በበሕቅ ልሕቀ - በየጥቂቱ አደገ”
·
ለእናቱና ለቤተሰቦቹ መታዘዝ “እንዘ ይትኤዘዝ ለአዝማዲሁ- ለቤተሰቦቹ እየታዘዘ አደገ” እንዲል።